ዓላማ -
በእስራኤል ውስጥ እያንዳንዱ ወንድና ሴት አስፈላጊውን የጤና አገልግሎት ለመስጠት ነው ::፡፡፡፡
በእስራኤል ግዛት ውስጥ ጉልህ የሆነ የህክምና ኢፍትሃዊነት አለ፤ የህክምና ባለሙያ እና ማህበራዊ አገልግሎቶች ከህዝብ ተገልለዋል፡፡
ታማኝነት የጎደለው ስለሆነ ብዙውን ጊዜ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ በሽታዋች ህመም በመሰቃየት ከፍተኛ ስጋት ላይ ያሉ ተጋላጭ ናቸው፡፡
እነዚህ ሰዎች ኦፊሴላዊ የመኖሪያ ሁኔታ ሰለሌላቸው ነው ጎን ለጎን ሕይወት አድን ህክምናዎችና ምርመራዎች ለመቀበል ፍቃድ አላገ ም አይሆንም እየተባሉ ነው፡፡
ጤና መሰረታዊ የሰብአዊ መብት መሆኑን ጽኑ ከሚለው ጠንካራ እምነት የሃይፋ ቡድን የህክምና ባለሙያ ሀኪሞች ፣ ነርሶች ፣ ማህበራዊ ሰራተኞችና ፋርማሲስቶች ''ቨኣሃቭታ'' ክሊኒክ አቋቁመዋል፡፡ በአጠቃላይ በእስራኤል በተለይም በሃይፋ ውስጥ መሰረታዊ እና አስፈላጊ ሕክምናዎች ለተነፈጉ ሁሉ እኩልና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ያለ ክፍያ በነጻ ለማቅረብ ያለመ “ፍቅር” ክሊኒክ ነው፡፡
ክሊኒኩ - ሙሉ በሙሉ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረት - በእስራኤል ውስጥ ከትውልድ አገሩ በመፈናቀል ምክንያት መደበኛ የመኖሪያ ፈቃድ ለተነፈጉ ሰዎች አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ክሊኒኩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ለእነዚህ የተገለሉ ቡድኖች ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሰጪ ሆኗል፡፡ የክሊኒኩ ሠራተኞች ሁሉንም ዓይነት እንክብካቤና አስፈላጊ የሕክምና እርዳታዎች ሙሉ በሙሉ በፈቃደኝነት ለማቅረብ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ እርዳታ የሚጠይቅ ማንኛውም ሰው በደስታ ፣ በእቅፍ፣ እና ከሁሉ የተሻለውን መልስ ለመስጠት ካለው ሙሉ ፍላጎት ጋር ነው፡፡
የክሊኒኩ ዋና ቡድን እንደ አስፈላጊነቱ ጊዜያቸውንና ሙያዎቻቸውን በፈቃደኝነት የሚሰጡ ብዙና ልዩ ልዩ ባለሙያዎችን ሰብስቧል፡፡
በክሊኒኩ ውስጥ እነዚህ በሙያቸው የተሻሉ ምርጥ ባለሙያዎችንና አገልግሎት ሰዋችን ያካትታሉ፡፡ የቤቴ የሆስፓታል ውስጥ የመምሪያ ኃላፊዎች ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ላብራቶሪ አገልግሎቶች ፣ የምስል እና የራዲዮሎጂ አገልግሎቶች እና ሌላው ቀርቶ ሆስፒታል መተኛት - ሁሉም በፈቃደኝነት ወይም በድጎማ መሠረት.